ለደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ወኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ምእምናን
እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ በሰላም አሸጋገራችሁ
በጎ ሥራ ለሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናና ክብር ሰላምም ይገባቸዋል ሮሜ 2 ቁ 10
በአለፈው 09/09/23 ቅዳሜ ለቤተ ክርስቲያናችን ገቢ ማሰባሰቢያ (ፈንድ ሬዚንግ ) ዝግጅት ማድረጋችን ይታወሳል በሁላችሁም ትብብር ዝግጅታችን በአማረ ሁኔታ ከአሰብነው በላይ ውጤታማ ሆኖልናል ስለዚህ ሁሉ ነገር የሆነው ያማረው በእናንተ ጠንካራ ትብብርና ተሳትፎ ነው ሁላችሁም ስላደረጋችሁት አስተዋጽኦ የዝግጅት ኮሚቴው በቅዱስ አማኑኤል ወኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ስም እግዚአብሔር ይስጥልን በማለት ምስጋና ያቀርባል
የደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ወኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ልማትና ዕቅድ ኮሚቴ