ጉዳዩ ዐሥራት በኩራት ስለመጠየቅ

ለደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ወኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ምእመናን በሙሉ፣

በቅርቡ የተከሰተውን የኮረናቫይረስ ወረርሽኝ አስመልክቶ በመላው ዓለም የተፈጠረውን ሁለንተናዊ ቀውስ ሁላችንም የምናውቀው ነው።በመሆኑም በሀገረ አሜሪካ ከመደበኛ ሥራቸው ለተፈናቀሉና በአነስተኛ የንግድ ሥራ ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶች መንግስት ተገቢውን የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ከውሳኔ ላይ የደረሰ ቢሆንም በዚህ እረገድ እስካሁን የእምነት ተቋማትን በተመለከተ መደበኛ መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲያቋርጡ ከመደረጋቸው ያለፈ ምንም ዓይነት የገንዘብ ድጋፍ አልተደረገልንም።

ስለሆነም ይህን ቤተክርስቲያን በናንተ ውድ ምእመናን ብርቱ ጥረትና ህብረት ከገዛነው ገና የወራት እድሜ ያስቆጠረ በመሆኑ የሚገጥመንን የገንዘብ እጥረት ለእናንተ መንገር ለቀባሪው ማርዳት ስለሚሆንብን የፈጣሪ ፈቃዱ ሆኖ በተከበረው የእምነት ቤታችን እስከምንሰባሰብ ድረስዐሥራት በኩራታችሁንበዚሁ በኩል በከፈትነው ድህረ ገፅ በመግባት ክፍያችሁን ለመክፈል እንደምትችሉ እያሳሰብን በቼክ ክፍያ ለመፈፀም የምትሹ ከዚህ በታች በተገለፀው የቤተክርስቲያናችን አካውንት ስም ማስተላለፍ ትችላላችሁ፣

DGK AMANUEL & KIDANE MEHRET ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH

በማለት ቼኩን መፃፍ ስትችሉ የፖስታ የመላኪያ አድራሻው

14-16 SOUTH MORTON AVE, MORTON,PA 19070

በማለት መላክ የምትችሉ ሲሆን በተጨማሪም ሌላው የመላኪያ አማራጭ DONATE NOW የሚለውን በመጫን በክሬዲት ካርድ ወይንም በፔፓል መክፈል የምትችሉ መሆናችሁን በቅዱስ አማኑኤል ወኪዳነ ምህረት ሥም የዐሥራት በኩራት ግዴታችሁን ትወጡ ዘንድ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።

አምላክ ጭንቀታችንን እና ፀሎታችንን ሰምቶ ከመጣብን መቅሰፍት ይታደገን ዘንድ ፈቃዱ ይሁን።

ወሰብሐት ለእግዚሐብሔር የደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ወኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን